Features Al Furqan አል ፉርቃን (pro)
ከሃምሳ ዓመት በፊት በሸኽ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ እና በሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ የቀረበው የክቡር ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም፤ እንሆ በወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ድምፅ ተዘጋጅቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቅዱስ ቁርኣንን ትርጉም ማድመጥ ለሚፈልጉ አመቺ ኾኖ ቀርቧል። የድምፅ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በዚህ መተግበሪያ ላይ ይገኛል።በዚህ አጋጣሚ እንደ አላህ ፈቃድ ሥራችንን ከእንከን የጠራ ለማድረግ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና ጥንቃቄ ጥረት ያደረግን ቢኾንም፤ ሰዎች ነንና ልንሳሳት እንደምንችል እናምናለን። በመኾኑም ይህ ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የቅዱስ ቁርአን ትርጉም እንደመኾኑ በማድመጥም ኾነ በማንበብ ሂደት ውስጥ የሚታያችኹን ክፍተት እንድተጠቁሙን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።ይህን ታላቅ ሥራ አኑረው ያለፉ አባቶቻችንንና ከህትመት እስከ ስርጭት የደከሙ ወንድምና እህቶችን ኹሉ ለሠሩት መልካም ሠራ ምንዳውን ያብዛላቸው። እኛንም በሰማነው የምንጠቀም ያድርገን። አሚን!!
Secure & Private
Your data is protected with industry-leading security protocols.
24/7 Support
Our dedicated support team is always ready to help you.
Personalization
Customize the app to match your preferences and workflow.
See the Al Furqan አል ፉርቃን (pro) in Action
Get the App Today
Available for Android 8.0 and above